[Author's Home Page]    [News Page]     Welcome:    ---    LOGIN
 Welcome to My Poetry Site      18899 Poems Read


ፍቅረኞች ሲጋቡ


 
ፍቅር እስተአፉ ሞልቶ ሲፈስ፣
እንዴት እንደዚህ ያለ መንፈስ፣
የመፍለቅለቅ ስሜት የሚያጭር፣
ሐሴት የሆነ ሚስጢር፣
ልባችሁ አጭቆ እንደሚያምቅ፣
ይላችኋል ድንቅ!
 
አጥብቃችሁ ይዛችሁት፣
አትፈቅዱም ልትለቁት፣
በምትሐቱ የፀሐይ ጨረር
በደንብ ለመንሸርሸር!
 
ፍቅር ቢሆንም ስሜት የፍንደቃ
ነገር ነው ቶሎ የሚነቃ -
እንደ ድርጭት ክንፍ መሳይ፣
ወይ እንደ ሸረሪት ድር
በዳመና አልባ ሰማይ!
 
ለዘላቂ ፍቅር ጥሬ እቃ፣
መሸመቺያ ትክክለኛ ወቅት
ወይ ደቂቃ፣
ልብ ዘና ሳይል በሙዚቃ!
 
የጋብቻችሁ
የፀሐይ ብርሃን ወቅት
ወይ የጫጉላ ሽርሽር፣
ሲቀየር ወደ ውሽንፍር፣
እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ፣
ወጀብ ትቋቋማላችሁ!
ደግሞም ተደጋግፋችሁ፣
ቀጥ ያለ ዳገት ትወጣላችሁ፣
መብረቅ ሲያጓራ በላያችሁ -
በሰማያዊ እርዳታና ፍቅር
በእምነትና ተስፋ ጭምር!
 
የወይን ብርጭቆ ማጋጨት፣
የአበባ እቅፍ መሠጣጠት፣
የፍቅርን ህልም
እውን አያደርገውም በውነት!
 
የሚጋሩት ችግር
የእንባ ዘለላ መስዋዕትነት፣
ያስፈልጋል ለፍቅር ውበት፣
ሙቀት ደሞም ድምቀት ለመስጠት!
ምድራዊ ሐሴት ነገር፣
ወደሰማያዊ ፀጋ ለመቀየር!
(በሄለን ስቲነር ራይስ፣ ትርጉም ዓለም ኃይሉ,

  Poetry Ad-Free Upgrades  




Vote for this poem

Please Comment On This Poem

Comments

 Email Address

 

Vote for this poem



Sign Guestbook Read Guestbook

valentine3

valentine3

valentine3
  [ Poetrypoem.com ]   [ Privacy ]   [Terms ]    [ Start a Free Site ]   [ My Poetry List ]
     ©2000 - 2022 ---------- Individual Authors of the Poetry.   All rights reserved by authors. 
wordrider1     author3578      dcdrifter      poetry2071      kuopenyung  View All Poets
Newest Item: Dont forget
Dont forget God loves you. ... More
Added: 2023-12-24  My Poetry List  PoetryPoem.com      Get a Free Site       Blogs     Stories     Premium Sites