Superimposed
Adorned to kill
The immaculate
It is unorthodox
Hewed out of a chocolate
Poetry Poem
What a trick
More Poetry >>
|
ያ የከንፈር ማህተም
ከዚህ አለም ተለይተህ'
ፀጥ ረጭ ብለህ'
ከፊቴ ተዘርግተህ ሳለህ'
አልሞከርኩም ምንም
የማይላወሱ ከንፈሮችህን ልስም !
ላይ በአፀዳ ነፍስ ሆነህ'
ያሳለፍናቸውን የፍቅር ዓመታት አስበህ'
ይሆን ታዝበህ?
ወስደህ ይሆን ግምት'
ስታገኘኝ ያለወትሮዬ ጭምት'
በጣቶቼ ጫፍ እንኳ '
የወደድኩትን የማልነካ?
ግና በመጨረሻ ስትስመኝ
ታስታውስ ይሆን ምን እንዳልከኝ?
"ውሰጅ ይህን
የከንፈር ማስታወሻ
ተቃርቧል የኔ መጨረሻ!"
"በፍቅራችን የጨለማ ሰዓት'
ምልክት ይሁንሽ ምናልባት'
መልሰሽ እስክትሰጪኝ
አንድ ብሩክ ጠዋት ስታገኚኝ!"
ያልዳበስኩ ለዚያ ነው!
ግን እንዳልከው'
ወደኋላ ተመልሼ'
መልእክቱን አስታውሼ'
ያን የመሰነባበቻ የከንፈር ማህተም
ልክ ከንፈሬ ላይ እንዳሳረፍኩ'
ከነግለቱ ይº¬ ነው' የምዘልቀው!
(ጁሊያን ካርሎሊን
Vote for this poem
ያ የከንፈር ማህተም
|
|
|
|
|
|
|
©2000 - 2022 ------- Individual Authors of the Poetry. All rights reserved by authors
Sign Guestbook
Read Guestbook
|
|
[ Control Panel ]
Last 100 Poems
|